የጥራጥሬ እህሎች ኮንፈረንስ !

  • Life style
None

ከእለታት አንድ ቀን ጥራጥሬዎች ታላቅ ኮንፈረንስ አዘጋጅተው ለስንዴ እንዲህ የሚል......


ከእለታት አንድ ቀን ጥራጥሬዎች ታላቅ ኮንፈረንስ አዘጋጅተው ለስንዴ እንዲህ የሚል መልእክት መጣላት:- "በንጉሥ ፊት ትቀርቢያለሽ"

እናም ስንዴ በወቅቱ የተነገራት መልእክት እያወጣች እያወረደች ስለ ጓደኞቿ ጥራጥሬዎችም እያሰበች ስለ እድለኛነቷ እጅግ ተደንቃ ሳትጨርስ በሰላም ከተቀመጠችበት መጋዘን አውጥተው ወደ ትልቅ ማሳ ወስደው በእርሻው ላይ በትነው ዘሯት የጠበቀችው የንጉሥ ፊት ቢሆንም የገጠማት ግን በመሬት ወስጥ ገብቶ መመበስበስ ነበር በዚህ ሁኔታ ወስጥ እያለች እንደገና አቆጥቁጣ በቀለች እንደገና የተነገራትን ንጉሥ ፊት ልቀርብ ነው እያለች አድጋ ብዙ ፍሬ እንዳፈራች ማጭድ የያዘ ሰው መጣና አጭዶ ወደ አውድማ ይዞአት ሄደና እላይዋ ላይ የነበረው ገለባ እስኪለቃት ድረስ በትላልቅ በሬዎች ተረግጣ አቅሏን እስክትስት በአየር ላይ ተበተነች በሁኔታው ግራ ብትጋባም ንጉሥ ፊት መቅረቧን እያሰበች ተፅናናች እናም በጆንያ(ማዳበሪያ) ተጭና የሞተር ጩኸት ወደሚያገሳበት ወፍጮ ቤት ተወሰደች እዚያ ወፍጮ ውስጥ ገበታ ተስፋዋ እስኪጨልም ተፈጨች ከዚያም ባለሙያ ሴቶች ተሽጣ ገባችና አንዴ በሙቅ በቀዝቃዛ ውሃ ነፍሷ እስኪጠፋ አሽተው አቦኩአት ትንሽ ቆይተውም በአንድ ትልቅ ገበር ምጣድ ላይ በኮባ ቅጠል ጠቅልለው ከላይና ከታች እሣት አንድደው አበሰሏት በመጨረሻም በሚያምር ሞሰብ ሸፋፍነው ወደ ንጉሥ ቤት ወስደው እንደ ተነገራት መልእክት በንጉሡ ፊት ቀረበች!

አንድ ሰው ወደ ተነገረለት ፍፃሜ እየገሰገሰ አያለሁ!

Language: Amharic
Categories: Life style

2 likes

Add comments

0 Comments

    No comments