">

እግዚአብሔር በእርግጥ ዝም ይላል?

  • Spritual
None

በብዙ ሰዎች ህይወት ውስጥ ከሚነሱ በርካታ ጥያቄዎች መካከል "እግዚአብሔር ለምን ዝም ይላል? " የሚለው አንዱ እና ዋንኛው ጥያቄ ነው። 

በብዙ ሰዎች ህይወት ውስጥ ከሚነሱ በርካታ ጥያቄዎች መካከል "እግዚአብሔር ለምን ዝም ይላል? " የሚለው አንዱ እና ዋንኛው ጥያቄ ነው ። በእርግጥ እግዚአብሔር ዝም ይላል? እግዚአብሔር ዝም ያለን የሚመስለንስ ለምንድን ነው ?

ግዚአብሔር በእርግጥ ዝም ይላል? 

ለዚህ ጥያቄ የእግዚአብሔር ቃል የሚሰጠው ምላሽ፥ 

“ስለ ጽዮን ዝም አልልም፥ ስለ ኢየሩሳሌምም ጸጥ አልልም፥ ጽድቅዋ እንደ ጸዳል መዳንዋም እንደሚበራ ፋና እስኪወጣ ድረስ።” ኢሳይያስ 62፥1
“እነሆ፥ የእግዚአብሔር እጅ ከማዳን አላጠረችም፥ ጆሮውም ከመስማት አልደነቈረችም፤” ኢሳይያስ 59፥1

2. እግዚአብሔር ዝም ያለ የሚመስለን ለምንድን ነው?

      እግዚአብሔር ዝም ያለን የሚመስለን፥

    2.1 ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ግንኙነት ሲቋረጥ፤

“ነገር ግን በደላችሁ በእናንተና በአምላካችሁ መካከል ለይታለች፥ እንዳይሰማም ኃጢአታችሁ ፊቱን ከእናንተ ሰውሮታል።” ኢሳይያስ 59፥2

    2.2 ድምጹን መስማት በማንችልበት ሁኔታ ውስጥ ስለምንሆን፤

በጭንቀት ውስጥ መሆን
ጥድፊያና ሁከት ውስጥ ስንሆን
ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ስንሆን ፥ በእነዚህ ሁኔታ ውስጥ ያለ ሰው እግዚአብሔር ዝም ያለው ሊመስለው ይችላል ።

3. ከዚህ በፊት በተናገረን ድምፅ ሳንታዘ ስንቀር ፤

4. የእግዚአብሔርን ድምጽ መለየት አለመቻል፤

     እያንዳንዳችን በቀን ውስጥ 60-70 ሺህ የሚጠጉ ሃሳቦች በአእምሮአችን ውስጥ ይመላለሳሉ ፥ ከእነዚህ ሃሳቦች ውስጥ ትክክለኛ የሆነውን የእግዚአብሔር ሃሳብን መለየት ካልቻልን እግዚአብሔር ዝም እንዳለን ልናስብ እንችላለን።


Language: Amharic
Categories: Spritual

2 likes

Add comments

0 Comments

    No comments