✨ ፍቅሩን እና ቸርነቱን ስበክ

✨ ፍቅሩን እና ቸርነቱን ስበክ
“ወይስ የእግዚአብሔር ቸርነት ወደ ንስሐ እንዲመራህ ሳታውቅ የቸርነቱንና የመቻሉን የትዕግሥቱንም ባለጠግነት ትንቃለህን?”— ሮሜ 2፥4
ወንጌልን ስንሰብክ በትክክል መናገር ያለብን ምንድን ነው?
ወንጌል የምስራች ነው !
- የእግዚአብሔር ጽድቅ መገኘትን ለመግለጥ እንጂ÷ ኢየሱስ ዓለምን ለመኮነን አልመጣም። መጽሐፍ እንዲህ ይላል፡- "ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ፥ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውም" (ዮሐ. 3፡17)።
ታዲያ ኢየሱስ ምን እንድናደርግ ነገረን?
ኢየሱስ የነገረን “ወንጌልን እንድን ሰበክ! ” ነው ።
ይኸውም እግዚአብሔር ምን ያህል ቸር፣ መሃሪና ይቅር ባይ እንደሆነ በጨለማው ዓለም ውስጥ ላሉ ሰዎች እንድንነግራቸው ነው። እርሱ የፍርድ አምላክ ብቻ ሳይሆን የፍቅር አምላክ ነው። ስለዚህ ፍቅሩን ስበክ። “የሚያቃጥል ሲኦል” የተሰኘው ፊልም ሰዎች ንስሐ እንዲገቡ በጊዜያዊነት በማስፈራራት ሊያነሳሳቸው ይችላል ሆኖም ግን ለተወሰነ ጊዜ ብቻ ነው። ፍርሃቱ ወደ ፊት ዘልቆ መሄድ ስለማይችል እውነተኛ ንስሃ ሰዎች መግባት አይችሉም ። ፍርሃቱ ሲለቃቸው በንሰሃ ፀንተው አይኖሩም። ወደ ቀድሞ ህይወታቸው ይመለሳሉ ። ምክንያቱም የእግዚአብሔር ቸርነትና ፍቅር ገብቶአቸው ሳይሆን በስሜት ላይ የተመሰረተ ንሰሃ ስለሆነ ነው።
ሰዎችን ወደ ንስሐ የሚመራው የእግዚአብሔር ቸርነት እንጂ የእግዚአብሔር ፍርድ አይደለም።
ሰዎች ስለ እግዚአብሔር ቸርነት ሲሰሙ፣ ከጨለማው ለመውጣት ይነሳሳሉ። ስለ ኖህ እናስብ ስለ መጪው ፍርድ ለዓመታት ሰበከ ነገር ግን ስንት ሰዎች ናቸው ንስሐ ገብተው አብረውት ወደ መርከብ የገቡት? ከቤተሰቡ በስተቀር ማንም ወደ መርከብ ለመግባት ፍላጎት አላሳየም። በሎጥም ዘመን እንዲሁ ተመሳሳይ ነበር። ነገር ግን ሐዋርያት ወንጌልን ሲሰብኩ የምሥራቹን ቃል የሰሙ አሕዛብ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በንስሃ ተመልሰዋል። ሃሌ ሉያ!
ወንጌል ÷በክርስቶስ የተስፋ፣ የፍቅር፣ የሕይወት የበረከት እና የድል መልእክት ነው። በእርግጥ ሲኦልና ገሃነም አለ። በተጨማሪም የእሳት ባህርም አለ÷ሲኦል እራሱ ከሰይጣን እና መዳንን ከሚቃወሙት ሁሉ ጋር ወደ እሣት ባህር ውስጥ ይጣላል እግዚአብሔር ግን የተባረከ ይሁን÷ በኢየሱስ የሚያምን ማንም ሰው ወደ ሲኦል እሄዳለሁ በማለት ሲኦልን መፍራት የለበትም ምክንያቱም ኢየሱስ ቀድሞውንም ወደ ሲኦል የገባው እኛን ከሲኦል ለማዳን ሲል ነው÷በድል እና በስኬት ለዘላለም ከእርሱ ጋር እንድንኖር ዋጋ ከፍሎ የዘላለምን ሕይወት ሰጥቶናል። በወንጌል ሕይወትንና ከሞት ፍርሃት ነጻ መውጣትን ለእያንዳንዳችን ሰጠን። ሃሌ ሉያ!
ጸሎት
ውድ አባት ሆይ፣ ስለ ጽድቅህ፣ ስለ ፍቅርህና ስለ ጸጋህ ወንጌል ስለ ምህረትህ አመሰግንሃለሁ። በሚሄድበት ሁሉ የቸርነትህን ብርሃን የሆነውን ወንጌል ለማስፋፋት የዚህ መልእክት ተሸካሚ መሆኔን አውጃለሁ ጌታ ሆይ ከጨለማው ኃይል ስላዳነከኝ እና ወደ ውድ ልጅህ መንግሥት ጠርተህ ስላስገባኸኝ አመሰግንሃለሁ። በክርስቶስ ኢየሱስ በሰጠኸኝ ድል እና የዘላለም ሕይወት ደስ ይለኛል።
ሃሌ ሉያ!
Language: AmharicCategories: Spritual
1 likes
No comments