ካነበብኩት ፅሑፍ ላይ የተወሰደ

ውድ ቤተሰብ ይህን ታሪክ ካነበብኩት ፅሑፍ ላይ የተወሰደ ሲሆን አስተማሪ ይሆናል ብዬ ስላሰብኩ ላካፍላችሁ ወደድኩ አንብቡትና የተሰማችሁን ሃሳብ በኮሜንት ላይ ጻፉ መልካም ንባብ 🙏
የሞት ፍርድ የተፈረደበት ሰው ኑዛዜ ! በእስር ቤት ውስጥ ሞት የተፈረደበት እስረኛ ÷በኤሌክትሪክ ወንበር ላይ ተቀምጦ በኤሌክትሪክ ከመያዙ በፊት የመጨረሻ መናገር የሚፈልገው ነገር ካለ ምኞቱን እንዲናገር እድል ተሰጠው ፣ እርሱም እስክሪብቶ እና ወረቀት ጠየቆ የሚከተለውን ኑዛዜ በፅሑፍ እንዲህ ሲል አስቀመጠ :-
ውድ እናቴ ዛሬ ህጉ ፍትሃዊ ቢሆን ኖሮ በኤሌክትሪክ ወንበር ላይ አጠገቤ ተቀምጠሽ እንደ እኔ በኤለክትሪክ መሰቃየትና ሞት ይጠብቅሽ ነበር ÷ ነገር ግን ህጉ አይነ ስውር ስለሆነ አብረን በሰራነው ወንጀል እኔ ዛሬ ሞት ተፈርዶብኛል።
እማዬ እንዴት እንደ ጀመረ ታስታውሻለሽ? እስቲ ከመሞቴ በፊት እኔ ላስታውስሽ ÷
የ 3 አመት ልጅ ሳለሁ የወንድሞቼን ጣፋጭ ስሰርቅ ታስታውሻለሽ? ያን ጊዜ አላስተካከልሽኝም ÷የ5 አመት ልጅ እያለሁ የጎረቤቶቼን አሻንጉሊቶች ሰርቄ ቤት ውስጥ የደበቅኩ ጊዜ ምንም እንዳልተናገርሽኝ አሁን ያለሁበት ሁኔታ አስታወሰኝ ÷ገና 12 አመቴ ነው በቤት ውስጥ ከተጫወትን በኋላ የአክስቴን ልጅ ኳስ ጋራጅ ውስጥ ስደበቅው አሁንም አይተሽኝ ነበር ነገር ግን በዝምታ ነው ያለፍሽኝ። በ15 ዓመቴ ከትምህርት ቤት የተባረር ኩበትን ቀን ታስታውሻለሽ? አባዬ ሊያስተካክለኝ ፈልጎ ነበር ÷አንቺ ግን እምቢ አለሽ እና በዚያው ቀን ስለዚህ ጉዳይ ከአባቴ ጋር መራራ የሆነክርክር ፈጠርሽ ምክንያቱም አንቺ እኔን ለመከላከል ገና ወጣት ነው በማለቷ ስትከራከሪ እንደነበር አስታውሳለሁ። አስተማሪዬ ክፍል ውስጥ አልማርም ብሎአል ስትልሽ÷ አንቺ ግን የኔ ልጅ ጎበዝ ተማሪ ነው ስህተት ነው ይህን አያደርግም በማለት የተናገርሽውንም አስታወስኩ ÷ይሁን እንጂ ጎበዝ ተማሪ አለመሆኔን ታውቂ ነበር ÷እነርሱ ግን ትክክል ነበሩ። እማዬ በደንብ ታስታ ውሻለሽ ÷በ17 ዓመቴ የጎረቤቶቻችንን ብስክሌት ስሰርቅ አይተሽኝ ነበር ÷ ነገር ግን እንደሸጥኩት እያወቅሽ ዝም አልሽ እንጂ አልነገርሻቸውም።እማ በጣም ወደድሽኝ አዎ ትወጂኛለሽ ነገር ግን አላስተካከልሽኝም። ይልቁንም አበላሽሽኝ። የኔ ጥፋተኝነት ሲጀምር እንደዚህ ነበር የጀመረው ÷ቀስ ብሎ አድጎ ግን ዛሬ በፈጸምኩት የባንክ ዘረፋና የነፍስ ግድያ ወንጀል ምክንያት በጭካኔ በኤሌክትሪክ ሾክ ሞት እንድቀጣ ተፈረደብኝ ። እናቴ በጣም ትንሽ በነበርኩበት ጊዜ ያንቺ መመሪያ ያስፈልገኝ ነበር፣ አሁን ግን ይህን መልእክት በምታነቢበት ጊዜ የሞት ቅጣቴን ተቀብዬ እሞታለሁ።
ያንቺ የእውነት የፍቅር ልጅሽ ነኝ !
ውድ አንባቢ ለሁሉም ወላጆች መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል:- “በበትር ከመምታት የሚራራ ሰው ልጁን ይጠላል፤ ልጁን የሚወድድ ግን ተግቶ ይገሥጻዋል።”
— ምሳሌ 13፥24
ከላይ ያነበባችሁት ታሪክ ምን አስታወሳችሁ? ትውስታችሁን በኮሜንት አካፍሉ ÷ መልካም ቀን!
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!
Language: AmharicCategories: Spritual
0 likes
No comments