" ጎበዝ እንንቃ እንጂ! "

መንፈሳዊ አለም ውስጥ እረፍት የለሽ እንቅስቃሴ መኖሩን ታውቃላችሁ?
1)ቅዱሳን መላእክት በእግዚአብሔር ፊት÷ ያለ እረፍት ያመልኩታል ።
“አራቱም እንስሶች እያንዳንዳቸው ስድስት ክንፎች አሉአቸው፥ በዙሪያቸ ውና በውስጣቸውም ዓይኖች ሞልተው ባቸዋል፤ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የነበረውና ያለ የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ እያሉ ቀንና ሌሊት አያርፉም።” ራእይ 4፥8
2) ዲያብሎስ በታላቅ ቁጣ በምድር ላይ ያሉ አማኞች ለመዋጥ ያለ እረፍት ይዞራል
“በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤” 1ኛ ጴጥሮስ 5፥8
“ስለዚህ፥ ሰማይና በውስጡ የምታድሩ ሆይ፥ ደስ ይበላችሁ፤ ለምድርና ለባሕር ወዮላቸው፥ ዲያብሎስ ጥቂት ዘመን እንዳለው አውቆ በታላቅ ቍጣ ወደ እናንተ ወርዶአልና።” ራእይ 12፥12
እኛም አማኞች ሳንዘናጋ እግዚአብሔርን ሁልጊዜ ያለማቋረጥ በልባችን እናምልክ ÷ በዲያብሎስ ወጥመድ ሃሳባችን እንዳይያዝ ሁልጊዜ የነቃን እንሁን!!
Language: EnglishCategories: Spritual
0 likes
No comments